Home | Amharic

ተልዕኮ

የህዝብ ምክር ቤት ጽ/ቤት (OPC) እራሱን የቻለ/ገለልተኛ የኮሎምቢያ ዲሰትሪክት አስተዳደር ኤጀንሲ ነው።

ከኖቨምቤር 1 ቀን 2022 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነው፣ የ OPC ቢሮ ወደ፦655 15th Street NW,
Suite 200, Washington DC, 20005-5701 ተዛውሯል።
ሁሉም መላላኮች ወደዚህ ወደ አዲሱ አድራሻ መሆን አለበት። በሽግግሩ ጊዜ የ OPCን ሠራተኞችን
ለማግኘት፣ ሁሉም ስልክ ቁጥሮች እና የሠራተኞች ኢሜይል አድራሻዎች ተመሳሳይ ናቸው።
በሚላክበት አድራሻ ምንም ዓይነት ሥራ አይሰራበትም፣ 1133 15th Street NW። አዲሱ ቢሮዎች
በሚከፈትበት ጊዜ በመጠቀምያዎች-ውስጥ ለመሄድ የደንበኛ ድጋፍ ሰጪን ለማግኘት ሕዝቡ በዚህ
ዌብሳይት እና በሌሎች የመገናኛ መንገዶች ይመከራሉ።

በሕግ OPC በዲስትሪክቱ ውስጥ የተፈጥሮ ጋዝ፣ የኤሌክትሪክ፣ ውሀ፣ የመስመር ስልክ አገልግሎቶች ተጠቃሚዎች ጠበቃ ነው። የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ህግ ቢሮውን በማህበረሰብ አገልግሎት ኮሚሽን ፊት ለሚካሄዱ ለሁሉም ከአገልግሎት ጋር ተያያዥ ክርክሮች ተከራካሪ ወገን አድርጎ ሾሞታል። ቢሮው በተጨማሪም በፌደራል ተቆጣጣሪ ድርጅቶች ስር የዲስትሪክቱን የተመን ከፋዮች ጥቅሞች ወክሎ ይቀርባል።

OPC የህዝብ ምክር ቤት አባል Sandra Mattavous–Frye፣ በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ካውንስል አማካሪነትና ፍቃድ በከንቲባው ለአራት አመታት የስራ ዘመን የተሾሙ ጠበቃ ይመራል።

ተጨማሪ ለማወቅ ለOPC ይደውሉ!

ይህን ያውቃሉ?…

OPC በሚከተሉት የአገልግሎት ጉዳዮች ላይ ሊረዳዎ ይችላል፡

የአገልግሎት መቋረጥ

የአገልግሎት ቅሬታዎች

የማጭጭርበርና አዋኪ ገበያዎች

የሶስተኛ ወገን አቅራቢዎች

የአገልግሎት ክፍያ አለመግባባቶች

የክፍያ ዝግጅቶች

የሀይል አጠቃቀም ውጤታማነት

የሸማች ትምህርት

የሶላር ሀይል ምንጮች

ለተጠቃሚዎች ህጋዊ መብቶች (Pepco፣ ቴሌኮሙኒኬሽን እና Washington Gas Light)

አገልግሎት መጀመር

የአገልግሎት ተወካዮች ለተጠቃሚዎች መታወቂያቸውን ማቅረብ አለባቸው። §313.1

አገልግሎቶች ለመጠየቅ የማህበራዊ ዋስትና ቁጥሮች አያስፈልጉም። §308.1

አገልግሎት ሰጭዎች የመጀመሪያ ጊዜ ሸማቾችን የዋስትና ተቀማጭ እንዲከፍሉ መጠየቅ አይችሉም። §307.7

ክፍያ

ሸማቾች በእያንዳንዱ የክፍያ ዙር ቢያንስ አንድ ጊዜ የክፍያ ደረሰኝ ማግኘት አለባቸው። §304.1

የአገልግሎት መቆራረጥ

አገልግሎቶች ሊቋረጡ የሚችሉ ቢሆንም አንድ ሸማች የተወሰኑ የጤና ችግሮች ካሉበት መቋረጡ እስከ 21 ቀናት መራዘም የለበትም። §311.1

አገልግሎቶች ብሔራዊ የአየር ንብረት አገልግሎት የሙቀት መጠኑ 2 ዲግሪ ወይም ከዚያ በታች የሚሆንበት የየትኛውንም ቀን ትንበያ ከሰጠ ከ24 ሰአት በኋላ ሊቋረጡ አይችሉም። §310.3

የአገልግሎት መመለስ

አንዴ አገልግሎት የተቋረጠበት ምክንያት ከተፈታ በኋላ አገልግሎቱ በ24 ሰዐት ውስጥ ተመልሶ ይቀጠላል። §315.1

ተጠቃሚዎች የአለምባባት ጉዳዮችን በማህበረሰብ አገልግሎት ኮሚሽን ችሎት ፊት የማሰማት መብት ያላቸው ሲሆን OPC የህግ እገዛ ሊያቀርብ ይችላል።

የሶስተኛ ወገን አቅራቢዎች

የግድ መቀየር አይኖርብዎትም። በአሁኑ የኤሌክትሪክ ወይም የተፈጥሮ ጋዝ አገልግሎትዎ ደስተኛ ከሆኑ የትኛውንም እርምጃ መውሰድ አይጠበቅብዎትም። “አገልግሎትዎ የመቋረጥ” አደጋ ውስጥ መሆኑን ወይም ይህ የመቀየሪያ ቀነ ገደብዎ መሆኑን የተመለከቱ የማስጠንቀቂያ ማስታወቂያዎች በጥንቃቄ ይገንዘቡ። ሁልጊዜም የትኛውንም አቅርቦቶች ለማጥናት ጊዜ ይስጡ።

ማጭበርበሮችን ይወቁ!

ማሳሳት አጭበርባሪዎች ትክክለኛውን የስልክ ጥሪያቸውን ምንጭ ህጋዊ ስለልክ ቁጥርን በመቅዳት ሲደብቁ ይፈጠራል።

ሌሎች የማጭበርበር ዘዴዎች የሽያጭ ሰራተኛ ወደ መኖሪያ ቤት ለመግባት በሚሞክርበት ወቅት የአገልግሎት ሰራተኛ መስሎ መቅረብን፣ ለደንበኛ ቅናሽ የአገልግሎት ተመኖች የሚያቀርቡ እና ለነባር ደንበኞች ‹‹ኩፖኖች ወይም ልዩ የሀይል ተመኖች›› የሚያቀርር የሮቦት የስልክ ጥሪዎችን ያጠቃልላሉ።

ፍጥነቱ ምንም ይሁን ምን በቀጥታ የሚያነጋግሩት የአገልግሎት ኩባንያዎን ተወካይ መሆኑን ከማረጋገጥዎ በፊት በፍጹም የአገልግሎት ሂሳብ መረጃዎችን፣ የማህበራዊ ዋስትና ቁጥርዎን፣ ሌላ የግል መረጃዎን ወይም በአካል ወይም በስልክ ለሚያነጋግርዎ ሰው ክፍያ መስጠት የለብዎትም።

ለዲሲ ተጠቃሚዎች የሶላር ተደራሽነትን ማስፋፋት

የሶላር ሀይል ሲስተም የሚገነባባቸው እና የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግባቸው የተለያዩ ዘዴዎች አሉ። የሶላር ፓኔሎችን መግዛት ወይም መከራየት እና ጣሪያዎ ላይ ለመስቀል ሊፈልጉ ይችላሉ።
የራስዎ መኖሪያ ቤት ከሌሉዎ ወይም መኖሪያ ቤትዎ ለሶላር ፓኔሎች አመቺ ካልሆነ በማህበረሰብ ሶላር ስር መሳተፍ ይችላሉ። የማህበረሰብ ሶላር የተለያዩ ሸማቾች ከአንድ ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ እና የሶላር ሀይል ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን በጋራ የሚጠቀሙበት ዝግጅት ነው።የቤት ባለቤት ከሆኑ በሶላር ሲስተም ገንዘብዎን ሊቆጥቡ ከሚችሉባቸው ዘዴዎች መካከል አንዱ በሶላር ማህበር አማካኝነት በጅምላ ግዢ ላይ መሳተፍ ነው። የሶላር ማህበራት የሶላር ፓኔሎችን ለማግኘት በጋራ ለመስራት የመኖሪያ መንደር የቤት ባለቤቶችን ያደራጃሉ።

የ DC Water ሸማች ህጋዊ መብቶች

OPC የ DC Water ተጠቃሚዎች እንደ ውሀ ሸማችነታቸው ያሏቸውን መብቶች እና ኃላፊነቶች እንዲያውቁ ይፈልጋል። የ DC Water ሸማች ህጋዊ መብቶች በ DC Water የሚቀርቡት አገልግሎቶች ለሁሉም የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ነዋሪዎች ወሳኝ እንደሆኑ እና በፍትሀዊነትና አሳማኝ ጊዜዎች ውስጥ መቅረብ እንዳለባቸው ይደነግጋሉ። ህጋዊ መብቶችን እዚህ ላይ ያንብቡ: https://bit.ly/3edYiXR.

የተገልጋዮች ማሳሰቢያ

 

ከዚህ በታች የተገለጹት በአገልግሎቶቻችን ላይ እርዳታ ለማግኘት ሊጠቀሟቸው የሚችሉ ጥቂት እጅግ ወሳኝ ሊንኮች ናቸው።

 

የህዝብ ምክር ቤት ጽ/ቤት/Office of the People’s Counsel|655 15th Street NW, Suite 500, Washington, DC 20005|ስልክ 202-727-3071|ፋክስ: 202-727-1014|TTY/TDD: 202-727-2876|Email: info@opc-dc.gov|ድረገጽ: www.opc-dc.gov|Facebook.com/DCPeoplesCounsel|Twitter @DCOPC|Instagram @DCOPC